am_tw/bible/kt/nazirite.md

1.2 KiB

ናዝራዊ፣ የናዝራዊ ስእለት

ናዝራዊ የሚባለው ናዝርውያን የሚሳሉትን ስእለት የተሳለ ሰው ነው።

  • የናዝራዊ እስለት ከማንኛውም ከወይን የተሠራ መጠጥም ሆነ ምግብ መታቀብን፣ በስምምነት እስከ ተወሰነ ቀን ድረስ ማለት ሳምንቶች ወይም ወሮች ሊሆኑ ይችላሉ ጠጕርን አለመስተካከልን ይጨምራል። ወደ ሞተ ሰው አካል እንዳይቀርብም ይከለከላል።
  • የተወሰነው ጊዜ ሲያበቃና ስእለቱም ሲፈጸም ናዝራዊው ወደ ካህን ሄዶ ቁርባን ያቀርባል። ጠጕሩን መቆረጥና ማቃጠልን ያካትትም ይሆናል። ሌሎች ገደቦች ሁሉ ይነሣሉ።
  • የናዝራዊ ስእለትን በተመለከተ ሳምሶን በጣም የታወቀ የብሉይ ኪዳን ሰው ነው።
  • መጥምቁ ዮሐንስም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የናዝራዊ ስእለት የነበረበት ሰው ሳይሆን አይቀርም።
  • ሐዋርያው ጳውሎስም አንድ ወቅት ላይ ይህን ስእለት ሳያደርግ አልቀረም።