am_tw/bible/kt/name.md

1.1 KiB

ስም

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም በተለያዩ ምሳሌያዊ አነጋገርና ጥቅም ላይ ውሏል።

  • በአንዳንድ ዐውዶች፣ “ስም” የሰውን ዝና ሊያመለክት ይችላል፤ ለምሳሌ፣ “ስማችንን እናስጠራው” እንደሚለው።
  • “ስም” የአንድ ነገር መታሰቢያን ሊያመለክትም ይችላል፤ ለምሳሌ፣ “የጣዖቶችን ስም ማጥፋት” ሲል ከእንግዲህ ማንም እንዳያስታውሳቸው ወይም እንዳያመልካቸው እንዚያን ጣዖቶች መደምሰስ ማለት ነው።
  • “በእግዚአብሔር ስም መናገር” እርሱን በመወከል በእርሱ ኀይልና ሥልጣን መናገር ማለት ነው።
  • የአንድ ሰው፣ “ስም” የሰውየውን ሙሉ ማንነት ሊያመለክት ይችላል፤ ለምሳሌ፣ “እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና” እንደሚለው።