am_tw/bible/kt/minister.md

10 lines
1.4 KiB
Markdown

# አገልጋይ፣ አገልግሎት
በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት “አገልጋይ” እና፣ “አገልግሎት” የተሰኙት ቃሎች እግዚአብሔርን በተመለከተ ሰዎችን በማስተማር፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸውም በማሰብ ሌሎችን መርዳት ማለት ነው። በዚህ መልኩ ሰዎችን የሚረዳ ሰው አገልጋይ ይባላል።
* በብሉይ ኪዳን ዘመን ለእርሱ መሥዋዕት በማቅረብ ካህናት ቤተ መቅደስ ውስጥ እግዚአብሔርን ያገለግሉ ነበር።
* አገልግሎታቸው የቤተ መቅደሱን ሥራ ማከናወንና ስለ ሌሎች ወደ እርሱ መጸለይህንም ያካትታል።
* በአዲስ ኪዳን፣ የውንጌል፣ “አገልጋይ” በኢየሱስ በማመን የሚገኘው የመዳንን ቃል ለሰዎች የሚያስተምር ሰው ነው። አንዳንዴ አገልጋይ፣ “ባርያ” ተብሎም ይጠራል።
* ሰዎችን የማገልገሉ ሥራ ስለ እግዚአብሔር ለሰዎች በማስተማር በመንፈሳዊ ሕይወታቸው መርዳትም ያካትታል።
* ለሕመምተኞች ጥንቃቄ በማድረግና ለድኾች ምግብ በመስጠት ቁሳዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን ማገልገልንም ያመለክታል።