am_tw/bible/kt/minister.md

1.4 KiB

አገልጋይ፣ አገልግሎት

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት “አገልጋይ” እና፣ “አገልግሎት” የተሰኙት ቃሎች እግዚአብሔርን በተመለከተ ሰዎችን በማስተማር፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸውም በማሰብ ሌሎችን መርዳት ማለት ነው። በዚህ መልኩ ሰዎችን የሚረዳ ሰው አገልጋይ ይባላል።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን ለእርሱ መሥዋዕት በማቅረብ ካህናት ቤተ መቅደስ ውስጥ እግዚአብሔርን ያገለግሉ ነበር።
  • አገልግሎታቸው የቤተ መቅደሱን ሥራ ማከናወንና ስለ ሌሎች ወደ እርሱ መጸለይህንም ያካትታል።
  • በአዲስ ኪዳን፣ የውንጌል፣ “አገልጋይ” በኢየሱስ በማመን የሚገኘው የመዳንን ቃል ለሰዎች የሚያስተምር ሰው ነው። አንዳንዴ አገልጋይ፣ “ባርያ” ተብሎም ይጠራል።
  • ሰዎችን የማገልገሉ ሥራ ስለ እግዚአብሔር ለሰዎች በማስተማር በመንፈሳዊ ሕይወታቸው መርዳትም ያካትታል።
  • ለሕመምተኞች ጥንቃቄ በማድረግና ለድኾች ምግብ በመስጠት ቁሳዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን ማገልገልንም ያመለክታል።