am_tw/bible/kt/lamb.md

1023 B

በግ፣ የእግዚአብሔር በግ

በግ ጥቅጥቅ ያሉ ለሱፍ መሥሪያ የሚያገለግሉ ጠጉሮች ያሉት ባለ አራት እግር እንስሳ ሲሆን፣ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይቀርባል። እርሱ ለሕዝቡ ኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ በመሞቱ ኢየሱስ፣ “የእግዚአብሔር በግ” ተብሏል።

  • በግ በቀላሉ የሚባዝን እንስሳ በመሆኑ ጥበቃና ክትትል ያስፈልገዋል። እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በበጎች መስሎአቸዋል።
  • ንጹሕና ጉድለት የሌለባቸው በጎችን ለእርሱ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ተናግሮአል።
  • ኢየሱስ ለሕዝቡ ኀጢአት ዕዳ ለመክፈል መሥዋዕት የሚሆን፣ “የእግዚአብሔር በግ” ተብሏል። እርሱ ምንም ኀጢአት የሌለበት በመሆኑ ፍጹምና ንጹሕ መሥዋዕት ነው።