# በግ፣ የእግዚአብሔር በግ በግ ጥቅጥቅ ያሉ ለሱፍ መሥሪያ የሚያገለግሉ ጠጉሮች ያሉት ባለ አራት እግር እንስሳ ሲሆን፣ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይቀርባል። እርሱ ለሕዝቡ ኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ በመሞቱ ኢየሱስ፣ “የእግዚአብሔር በግ” ተብሏል። * በግ በቀላሉ የሚባዝን እንስሳ በመሆኑ ጥበቃና ክትትል ያስፈልገዋል። እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በበጎች መስሎአቸዋል። * ንጹሕና ጉድለት የሌለባቸው በጎችን ለእርሱ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ተናግሮአል። * ኢየሱስ ለሕዝቡ ኀጢአት ዕዳ ለመክፈል መሥዋዕት የሚሆን፣ “የእግዚአብሔር በግ” ተብሏል። እርሱ ምንም ኀጢአት የሌለበት በመሆኑ ፍጹምና ንጹሕ መሥዋዕት ነው።