am_tw/bible/kt/kingofthejews.md

8 lines
978 B
Markdown

# የአይሁድ ንጉሥ
* የአይሁድ ንጉሥ” የተሰኘው የኢየሱስ የመሲሑ መጠሪያ ነው።
* ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው፣ “የአይሁድ ንጉሥ” የሆነውን ሕፃን ለመፈለግ ሰብዓ ሰገል ወደ ቤተ ልሔም የመጡ ጊዜ ነበር።
* ከእርሷ የሚወለደው ልጅ የንጉሥ ዳዊት ዘር እንደሆነና ለመንግሥቱም ፍጻሜ እንደሌለው መልአኩ ለማርያም ነግራት ነበር።
* ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት የሮም ወታደሮች እያፌዙ፣ “የአይሁድ ንጉሥ” በማለት ጠርተውታል። ይህ መጠሪያ እንጨት ላይ ተጽፎ ኢየሱስ የተሰቀለበት መስቀል ጫፍ ላይ እንዲሆን ተደርጎ ነበር።
* ኢየሱስ በእውነት የአይሁድ ንጉሥ ነው፤ እርሱ በፍጥረት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።