# የአይሁድ ንጉሥ * የአይሁድ ንጉሥ” የተሰኘው የኢየሱስ የመሲሑ መጠሪያ ነው። * ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው፣ “የአይሁድ ንጉሥ” የሆነውን ሕፃን ለመፈለግ ሰብዓ ሰገል ወደ ቤተ ልሔም የመጡ ጊዜ ነበር። * ከእርሷ የሚወለደው ልጅ የንጉሥ ዳዊት ዘር እንደሆነና ለመንግሥቱም ፍጻሜ እንደሌለው መልአኩ ለማርያም ነግራት ነበር። * ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት የሮም ወታደሮች እያፌዙ፣ “የአይሁድ ንጉሥ” በማለት ጠርተውታል። ይህ መጠሪያ እንጨት ላይ ተጽፎ ኢየሱስ የተሰቀለበት መስቀል ጫፍ ላይ እንዲሆን ተደርጎ ነበር። * ኢየሱስ በእውነት የአይሁድ ንጉሥ ነው፤ እርሱ በፍጥረት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።