am_tw/bible/kt/jew.md

8 lines
778 B
Markdown

# አይሁድ፣ አይሁዳዊ
አይሁድ በልጅ ልጁ በያዕቆብ በኩል የአብርሃም ዘር የሆኑ ሕዝብ ናቸው።
* ሰዎች እስራኤላውያን አይሁድ በማለት መጥራት የጀመሩት ከባቢሎን ምርኮ ወደ ይሁዳ ምድር ከተመለሱ በኋላ ነበር።
* “አይሁድ” የሚለው ቃል የመጣው ከ፣ “ይሁዳ” ነው። ወደ ባቢሎን የተወሰዱ እስራኤላውያን፣ ከደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት የመጡ ነበሩ።
* መሲሑ ኢየሱስ አይሁድ ነበር። ይሁን እንጂ፣ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን መቀበል አልፈለጉም፤ እንዲያውም እንዲገደል ጠየቁ።