am_tw/bible/kt/jew.md

778 B

አይሁድ፣ አይሁዳዊ

አይሁድ በልጅ ልጁ በያዕቆብ በኩል የአብርሃም ዘር የሆኑ ሕዝብ ናቸው።

  • ሰዎች እስራኤላውያን አይሁድ በማለት መጥራት የጀመሩት ከባቢሎን ምርኮ ወደ ይሁዳ ምድር ከተመለሱ በኋላ ነበር።
  • “አይሁድ” የሚለው ቃል የመጣው ከ፣ “ይሁዳ” ነው። ወደ ባቢሎን የተወሰዱ እስራኤላውያን፣ ከደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት የመጡ ነበሩ።
  • መሲሑ ኢየሱስ አይሁድ ነበር። ይሁን እንጂ፣ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን መቀበል አልፈለጉም፤ እንዲያውም እንዲገደል ጠየቁ።