am_tw/bible/kt/israel.md

10 lines
933 B
Markdown

# እስራኤል፣ እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሕዝብ
እስራኤል እግዚአብሔር ለያዕቆብ የሰጠው ስም ነው። እስራኤል፣ “ከእግዚአብሔር ጋር ታገለ” ማለት ነው።
* የያዕቆብ ዘሮች የእስራኤል ሕዝብ፣ ወይም እስራኤላውያን በመባል ታውቀዋል።
* እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ኪዳን አደረገ። እነርሱ የእርሱ የተመረጠ ሕዝብ ናቸው።
* እስራኤል የሕዝባቸው ስም ነው።
* የእስራኤል ሕዝብ ከአሥራ ሁለት ነገዶች የተገኘ ነው።
* ንጉሥ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ለሁለት መንግሥታት ተከፈለ፤ ደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት ሲባል፣ ሰሜናዊው መንግሥት የእስራኤል መንግሥት ተባለ።