am_tw/bible/kt/israel.md

933 B

እስራኤል፣ እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሕዝብ

እስራኤል እግዚአብሔር ለያዕቆብ የሰጠው ስም ነው። እስራኤል፣ “ከእግዚአብሔር ጋር ታገለ” ማለት ነው።

  • የያዕቆብ ዘሮች የእስራኤል ሕዝብ፣ ወይም እስራኤላውያን በመባል ታውቀዋል።
  • እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ኪዳን አደረገ። እነርሱ የእርሱ የተመረጠ ሕዝብ ናቸው።
  • እስራኤል የሕዝባቸው ስም ነው።
  • የእስራኤል ሕዝብ ከአሥራ ሁለት ነገዶች የተገኘ ነው።
  • ንጉሥ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ለሁለት መንግሥታት ተከፈለ፤ ደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት ሲባል፣ ሰሜናዊው መንግሥት የእስራኤል መንግሥት ተባለ።