am_tw/bible/other/winepress.md

7 lines
673 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ወይን መርገጫ
በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ወይን መርገጫ የወይን ጠጅ ለመሥራት የወይኑ ፍሬ የሚረገጥበት ቦታ ነው።
* የእስራኤል ወይን መርገጫ መሬት ላይ የተቆፈረ ትልቅ፣ ሰፊ ጉድጓድ ነበር። የወይኑ ዘለላዎች ታችኛው የጉድጓዱ ጠፍጣፋ ቦታ ላይ ይደረጉና የወይኑ ጭማቂ እንዲወጣ ሰዎች በእግራቸው ይረግጡት ነበር።
* ወይን መርገጫ የእግዚአብሔር ቁጣ ሕዝቡ ላይ መፍሰሱን ለማሳየት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።