am_tw/bible/other/watchtower.md

9 lines
1004 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መጠበቂያ ግንብ
“መጠበቂያ ግንብ” ጠባቂዎች እዚያ ላይ ሆነው ማንኛውንም አደጋ የሚመለከቱበት ቦታ እንዲሆን የተሠራ ረጅም ግንብ ነው። እነዚህ ግንቦች አብዛኛውን ጊዜ የሚሠሩት ከድንጋይ ነው።
* እነርሱ ላይ ሆነው እህላቸውን ሌቦች ከመሰረቅና ከእንስሳት ለመጠበቅ ባለ ርስቶችም መጠበዚያ ግንብ ይሠራሉ።
* ብዙውን ጊዜ ግንቡ ጠባቂዎቹ ከነቤተሰባቸው የሚኖርበት ክፍሎችም ይኖሯቸዋል፤ በዚህ ሁኔታ ለሊትና ቀን በጥበቅ ይተጋሉ።
* ጠላት ከተማዋን ለማጥቃት ሲመጣ ማየት እንዲቻል የከተማ መጠበቂያ ግንቦች ከከተማዋ በጣም ከፍ እንዲል ተደርጎ ይሠራል።
* መጠበቂያ ግንብ ከጠላቶች የመጠበቅና ከለላ የማግኘት ምሳሌ ነው።