am_tw/bible/other/shepherd.md

11 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# እረኛ
እረኛ በጎችንና እነርሱን የመሳሰሉ እንስሳትን የሚጠብቅ ሰው ነው
* እረኛ ለበጎቹ ይጠነቀቃል፤ መልካም ምግብና ውሃ ወዳለበት ቦታ ይመራቸዋል። እረኛ በጎቹ እንዳይጠፉም ይጠብቃል፤ ከዱር አውሬ ይጠብቃቸዋል
* ይህ ቃል ለሰዎች መንፈሳዊ ጉዳይ ማሰብን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ እንደ ተለዋጭ ዘይቤ ቀርቧል። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ለእነርሱ የተናገረውን ማስተማርን መሄድ በሚገባቸው መንገድ መምራትንም ይጨምራል
* ለእነርሱ የሚያስብና የሚጠነቀቅ በመሆኑ ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር የሕዝቡ፣ “እረኛ” ተብሏል። እርሱ ይመራቸዋል፤ ደግሞም ይከላከልላቸዋል
* ያህዌን እንዲይያመልኩ በመንፈሳዊ ደረጃ እነርሱን በመምራቱና ወደ ምድረ ከነዓን በሚያደርጉትም ጉዞ ይመራቸው ስለነበር ሙሴ የእስራኤላውያን እረኛ ነበር
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ፣ “መልካም እረኛ” በማለት ራሱን ጠርቷል።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ “እረኛ” የሚለው ቃል የአማኞች መንፈሳዊ መሪ የሆን ሰውን ያመለክታል። የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችና መጋቢዎችም እረኛ ተብለዋል