# እረኛ እረኛ በጎችንና እነርሱን የመሳሰሉ እንስሳትን የሚጠብቅ ሰው ነው * እረኛ ለበጎቹ ይጠነቀቃል፤ መልካም ምግብና ውሃ ወዳለበት ቦታ ይመራቸዋል። እረኛ በጎቹ እንዳይጠፉም ይጠብቃል፤ ከዱር አውሬ ይጠብቃቸዋል * ይህ ቃል ለሰዎች መንፈሳዊ ጉዳይ ማሰብን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ እንደ ተለዋጭ ዘይቤ ቀርቧል። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ለእነርሱ የተናገረውን ማስተማርን መሄድ በሚገባቸው መንገድ መምራትንም ይጨምራል * ለእነርሱ የሚያስብና የሚጠነቀቅ በመሆኑ ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር የሕዝቡ፣ “እረኛ” ተብሏል። እርሱ ይመራቸዋል፤ ደግሞም ይከላከልላቸዋል * ያህዌን እንዲይያመልኩ በመንፈሳዊ ደረጃ እነርሱን በመምራቱና ወደ ምድረ ከነዓን በሚያደርጉትም ጉዞ ይመራቸው ስለነበር ሙሴ የእስራኤላውያን እረኛ ነበር * አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ፣ “መልካም እረኛ” በማለት ራሱን ጠርቷል። * አዲስ ኪዳን ውስጥ “እረኛ” የሚለው ቃል የአማኞች መንፈሳዊ መሪ የሆን ሰውን ያመለክታል። የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችና መጋቢዎችም እረኛ ተብለዋል