am_tw/bible/other/perfect.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ፍጹም
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ፍጹም” የሚለው ቃል በክርስትና ሕይወታችን አስተዋዮችን በሳሎች ሆኖ መገኘትን ነው። አንዳንዴ “ፍጹም” የሚለው ቃል የተሟላና እንከን የሌለበት እስኪሆን ድረስ በክርስትና ሕይወት ማደግ ማለትም ይሆናል።
* አንድ ክርስቲያን ፍጹምና በሳል ሆነ ሲባል ታዛዥ፣ ኀጢአት የሌለው ሆነ ማለት ነው።
* “ፍጹም” “የተሟላ” ወይም፣ “ሙሉ” መሆን ማለትም ይሆናል።
* በመከራ መጽናት፣ አማኙ ውስጥ ሙሉነትንና ብስለትን እንደሚያስገኝ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የያዕቆብ መልእክት ይናገራል።
* ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ሲያጠኑና ለቃሉ ሲታዘዙ በባሕርያቸው ውስጥ ክርስቶስን እየመሰሉ ስለሚሄዱ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ሙሉና በሳሎች ይሆናሉ።