am_tw/bible/other/honey.md

11 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ማር፣ የማር እንጀራ
ማር ንቦች ከአበባ የሚሠሩት ጣፋጭና ሙጫነት ያለው የሚበላ ነገር ነው። የማር እንጀራ ንቦቹ ማሩን የሚያኖሩበት እንደ ሰም ያለው ቅርጽ ነው።
* እንደ ዐይነቱ ማር ቢጫማ፣ ወይም ቡኒ ዐይነት መልክ ይኖረዋል።
* በጣም ጣፋጭ ወይም በጣም አስደሳች ነገርን ለመወከል አንዳንዴ ማር በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል። አንዳንዴ ያ ጣፋጭና አስደሳች ነገር “ማር” ነው ሲባል፣ ሌላ ጊዜ፣ “እንደ ማር” ይባላል።
* አንዳንዴ ማር የዛፍ ሽንቁርን ወይም ንቦቹ መኖሪያ የሚያደርጉትን ዱር ቦታ ውስጥ ሁሉ ሊገኝ ይችላል። ሰዎች ለመብል ወይም ለመሸጥ ንቦች ያነባሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጥቀሰው ማር ግን የዱር ማር ሊሆን ይችላል።
* በጦርነት ጊዜ ኀይልና ብርታት ለማግኘት የሳኦል ልጅ ዮናታን ጫካ ውስጥ ያገኘውን የዱር ማር በላ።
* አንድ ጊዜ ሳምሶን የሞተ አንበሳ ውስጥ ማር አግኝቶ ነበር።
* በረሐ በነበረ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ አንበጣና ማር ይበላ ነበር።