# ማር፣ የማር እንጀራ ማር ንቦች ከአበባ የሚሠሩት ጣፋጭና ሙጫነት ያለው የሚበላ ነገር ነው። የማር እንጀራ ንቦቹ ማሩን የሚያኖሩበት እንደ ሰም ያለው ቅርጽ ነው። * እንደ ዐይነቱ ማር ቢጫማ፣ ወይም ቡኒ ዐይነት መልክ ይኖረዋል። * በጣም ጣፋጭ ወይም በጣም አስደሳች ነገርን ለመወከል አንዳንዴ ማር በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል። አንዳንዴ ያ ጣፋጭና አስደሳች ነገር “ማር” ነው ሲባል፣ ሌላ ጊዜ፣ “እንደ ማር” ይባላል። * አንዳንዴ ማር የዛፍ ሽንቁርን ወይም ንቦቹ መኖሪያ የሚያደርጉትን ዱር ቦታ ውስጥ ሁሉ ሊገኝ ይችላል። ሰዎች ለመብል ወይም ለመሸጥ ንቦች ያነባሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጥቀሰው ማር ግን የዱር ማር ሊሆን ይችላል። * በጦርነት ጊዜ ኀይልና ብርታት ለማግኘት የሳኦል ልጅ ዮናታን ጫካ ውስጥ ያገኘውን የዱር ማር በላ። * አንድ ጊዜ ሳምሶን የሞተ አንበሳ ውስጥ ማር አግኝቶ ነበር። * በረሐ በነበረ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ አንበጣና ማር ይበላ ነበር።