am_tw/bible/other/gnashteeth.md

7 lines
1.0 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጥርስ ማፋጨት
ጥርስ ማፋጨት ማለት ጥርሶችን በማያያዝ ወደ ፊት ወደ ኋላ በማድረግ ወይም ግራና ቀኝ በማድረግ እርስ በርሳቸው እንዲፋጩ ማድረግ ማለት ነው። ይህ ብዙውን ጊዜ የሚያሳየው ከባድ ስቃይን (ሕመምን) ወይም ቊጣን ነው።
* ገሃነም ውስጥ የሚኖሩ ከሚደርስባቸው ከባድ ስቃይ የተነሣ ጥርሳቸውን እንደሚያፏጩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
* የአገርህ ባሕል አንድ ሰው ሲቆጣ ጥርሱን የማያፋጭ ከሆነ ይህ ሐረግ፣ “በቍጣ ጥርስን ማፋጨት” ብሎ መተርጎም ይቻላል። ወይም በአንተ ባሕል ሰዎች ሲቆጡ የሚያደርጉትን እንደ እግርን አንስቶ መሬቱን በኀይል መርገጥን የላይ የታች ጥርሶችን ግጥም አድርጎ መያዝን ወይም መጮኽን የመሳሰሉ ቃሎች መጠቀም ይቻላል።