10 lines
1.2 KiB
Markdown
10 lines
1.2 KiB
Markdown
|
# ማክበር
|
||
|
|
||
|
አንድ ሰው ወይም ነገር ምን ያህል ታላቅና አስፈላጊ መሆኑን ማሳየት ወይም መናገር ማለት ነው። ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ክብር መስጠት” ማለት ነው።
|
||
|
|
||
|
* እርሱ ስላደረገው ድንቅ በመናገር ሰዎች እግዚአብሔርን ማክበር ይችላሉ።
|
||
|
* ለእርሱ ክብር በሚያስገኝ መንገድ በመኖርና እርሱ ምን ያህል ታላቅና ቸር መሆኑን በማሳየት እግዚአብሔርን ማክበርም ይችላሉ።
|
||
|
* መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ራሱን አከበረ ሲል ብዙውን ጊዜ በተአምራቱ አማካይነት አስደናቂ ታላቁነቱን አሳየ ማለቱ ነው።
|
||
|
* የወልድን ፍጹምነት፣ ውበትና ታላቅነት ለሰዎች በመግለጥ እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድን ያከብራል።
|
||
|
* በክርስቶስ የሚያምን ሁሉ ከእርሱ ጋር ይከብራል። ከሞት በሚነሡበት ጊዜ ክብሩን እንዲያንጸባርቁና ለፍጥረት ሁሉ ጸጋውን ለማሳየት ይለወጣሉ።
|