am_tw/bible/other/foundation.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መሠረት፣ መሠረተ
“መሠረተ” የሚለው ግሥ አንድ ነገር ላይ ሠራ ወይም ገነባ ማለት ነው። መሠረት አንድ ሕንፃ የሚያርፍበት ከታች ያለው አካል ነው።
* ሕንፃውን በሙሉ መሸከም እንዲችል የአንድ ቤት ወይም ግንባታ መሠረት በጣም ጠንካራ መሆን አለበት።
* “መሠረት” የሚለው ቃል የአንድ ነገር ጅማሬን ወይም አንድ ነገር የተፈጠረበትን ጊዜም ያመለክታል።
* በምሳሌያዊ አነጋገር በክርስቶስ የሚያምኑ ክርስቶስ ራሱ የማእዘን ራስ ከሆነበት፣ በነቢያትና በሐዋርያት ትምህርት ላይ ከተመሠረተ ሕንፃ ጋር ተመሳስለዋል።
* “የመሠረተ ድንጋይ” የመሠረቱ አካል የሆነ ድንጋይ ነው። መላውን ሕንፃ መሸከም የሚችሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ድንጋዮቹ፣ “የፈተናሉ” ወይም፣ “በተለያየ መከራ ያልፋሉ።”