am_tw/bible/other/foreigner.md

8 lines
860 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ባዕድ፣ መጻተኛ
“ባዕድ” ወይም “መጻተኛ” የሚለው ከራሱ አገር ውጪ የሚኖርን ሰው ያመለክታል። በተለይም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከራሱ ሕዝብ መካከል ወጥቶ ሌላ ሕዝብ ጋር የሚኖር ሰው ማለት ነው።
* መጻተኛ በቋንቋም ሆነ በባሕሉ የተለየ ሰው ነው።
* ክርስቶስን ከማወቃቸው በፊት ለእግዚአብሔር ኪዳን፣ “መጻተኞች” እንደ ነበሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች ይጽፋል።
* “መጻተኛ” የሚለውን ቃል፣ “ከሌላ አገር የመጣ” ብሎ መተርጎም ይቻላል፤ እንዲህ ሲባል ግን እናንተ የማታውቁት ሰው ሁሉ ማለት እንዳልሆነ መረዳት ይኖርባችኋል።