am_tw/bible/other/father.md

8 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# አባት፣ ጥንተ አባት
ቃል በቃል ከተወሰደ፣ “አባት” የአንድ ሰው ወንዱ ወላጅ ማለት ነው። ይህን ቃል በተመለከተ በርካታ ምሳሌያዊ አነጋገሮች አሉት።
* ብዙውን ጊዜ፣ “አባት” ወይም “ጥንተ አባት” የተሰኙ ቃሎች ጥቅም ላይ የሚውሉት በቀድሞ ዘመን የነበሩ ጥንታውያን ወላጆችን ለማማልከት ነው።
* “የ…አባት” የሚለው አገላለጽ የአንድ አገር መሪ ወይም መሥራችን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። ለምሳሌ ዘፍጥረት 4 ላይ፣ “እርሱም በድንኳን ውስጥ ለሚቀመጡ ሁሉ አባት ነበር” ሲል፣ “ድንኳን ውስጥ ለመኖር የመጀመሪያ ለሆኑት ሕዝቦች ጎሳ መሪ” ማለት ሊሆን ይችላል።
* ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌልን በማካፈል ክርስቲያን እንዲሆኑ የረዳቸው ሰዎች “አባት” በማለት በምሳሌያዊ መልኩ ራሱን ይጠራል።