am_tw/bible/other/exile.md

9 lines
870 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ምርኮ፣ ምርኮኛ
“ምርኮ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከአገራቸው ርቀው ሌላ ቦታ እንዲኖሩ የተገደዱ ሰዎችን ያመለክታል።
* ብዙ ጊዜ ሰዎች ለቅጣት ወይም በፖለቲካ ምክንያት ከአገር ውጪ እንዲኖሩ ይገደዳሉ።
* በጦርነት የተሸነፉ ሰዎች ለእርሱ እንዲሠሩ ተብሎ አሸናፊው ሰራዊት አገር ውስጥ እንዲኖሩ ይወሰዳሉ።
* የባቢሎን ምርኮ የሚባለው ብዙ የአይሁድ ዜጎች ከአገራቸው ተወስደው በባቢሎን እንዲኖሩ የተገደዱበት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ነው።
* “ምርኮኛ” የሚለው ቃል ከአገር ከወገናቸው ርቀው በባዕድ ምድር የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል።