9 lines
1.1 KiB
Markdown
9 lines
1.1 KiB
Markdown
|
# ቆጠራ
|
||
|
|
||
|
“ቆጠራ” የሚለው ቃል ሥርዓት ባለው መልኩ በአገሩ ወይም በመንግሥቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች መቊጠርን ያመለክታል።
|
||
|
|
||
|
* ብሉይ ኪዳን የእስራኤል ሰዎች እንዲቆጠሩ እግዚአብሔር በተለያየ ጊዜ አዝዞ እንደ ነበር መዝግቦአል፤ ለምሳሌ እስራኤል መጀመሪያ ከግብፅ ሲወጡና በኋላም ከነዓን ከመግባታቸው ጥቂት ቀደም ሲል።
|
||
|
* ብዙውን ጊዜ ቆጠራ የሚደረገው ግብር የሚከፍሉ ምን ያህል ሰዎች እንደ ሆኑ ለማወቅ ነበር።
|
||
|
* ለምሳሌ ከዘፀአት እንደምንመለከተው አንድ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ለመቅደሱ ሥራ የሚሆን ግማሽ ሰቄል እንዲከፍል ለማድረግ የእስራኤል ሰዎች ተቆጥረው ነበር።
|
||
|
* ኢየሱስ ሕፃን በነበረ ጊዜ መንግሥታቸው ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ ለማወቅና ግብር እንዲከፍሉ ለማድረግ የሮም መንግሥት የሕዝብ ቆጠራ አድርጎ ነበር።
|