# ቆጠራ “ቆጠራ” የሚለው ቃል ሥርዓት ባለው መልኩ በአገሩ ወይም በመንግሥቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች መቊጠርን ያመለክታል። * ብሉይ ኪዳን የእስራኤል ሰዎች እንዲቆጠሩ እግዚአብሔር በተለያየ ጊዜ አዝዞ እንደ ነበር መዝግቦአል፤ ለምሳሌ እስራኤል መጀመሪያ ከግብፅ ሲወጡና በኋላም ከነዓን ከመግባታቸው ጥቂት ቀደም ሲል። * ብዙውን ጊዜ ቆጠራ የሚደረገው ግብር የሚከፍሉ ምን ያህል ሰዎች እንደ ሆኑ ለማወቅ ነበር። * ለምሳሌ ከዘፀአት እንደምንመለከተው አንድ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ለመቅደሱ ሥራ የሚሆን ግማሽ ሰቄል እንዲከፍል ለማድረግ የእስራኤል ሰዎች ተቆጥረው ነበር። * ኢየሱስ ሕፃን በነበረ ጊዜ መንግሥታቸው ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ ለማወቅና ግብር እንዲከፍሉ ለማድረግ የሮም መንግሥት የሕዝብ ቆጠራ አድርጎ ነበር።