am_tw/bible/other/bronze.md

9 lines
982 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ናስ (ነሐስ)
“ናስ” - መዳብናን ቆሮቆሮን አብሮ በማንጠር የሚሠራ አንድ ዐይነት ብረት መሳይ ነገር ነው። ጥቁር ቡኒ መልክ ቢኖረውም በመጠኑ ወደ ቀይም ወሰድ ያደርገዋል።
* ናስ በውሃ መሸርሸርን ይከላከላል፤ ጥሩ የሙቀት አስተላላፊም ነው።
* በጥንት ዘመን ናስ መገልገያ መሣሪያዎችን፣ የጦር ዕቃዎችን፣ የቅርጽ ሥራዎችን፣ መሠዊያዎችን፣ ድስቶችን፣ የወታደር ትጥቆችን የመሳውሰሉ ነገሮችን ለመሥራት ያገለግል ነበር።
* የሐሰተኛ አማልክት ምስሎችም ከናስ ይሠሩ ነበር።
* የናስ ዕቃዎች የሚሠሩት በመጀመሪያ ናሱን በማቅለጥና ፈሳሹን ቅርጽ ማውጫ ላይ በማፍሰስ ነው። ይህ ሂደት፣ “ቅርጽ ማውጣት” ይባላል።