am_tw/bible/other/breastplate.md

7 lines
963 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጥሩር
ጥሩር የሚባለው በጦርነት ጊዜ ወታደሩን ለመከለል ደረትን የሚሸፍን መሥራሪያ ነው። እስራኤላዊው ሊቀ ካህን ይለብስ የነበረው ልዩ ዐይነት ልብስ ክፍል ጥሩር ይባል ነበር።
* ወታደሮች የሚጠቀሙበት ጥሩር ከእንጨት፣ ከብረት ወይም ከቆዳ ነበር የሚሠራው። ዓላማው ቀስት፣ ጦር ወይም ሰይፍ የወታደሩን ደረት እንዳይወጋው መከላከል ነበር።
* እስራኤላዊ ሊቀ ካህን የሚለብሰው ጥሩት ከጨርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የከበሩ ጌጣጌጦች ይያያዙበት ነበር። ቤተ መቅደሱ ውስጥ እግዚአብሔርን የማገልገል ሥራውን ሲያከናውን ካሁኑ ይህን ይለብስ ነበር። የሊቀ ካህኑ ጥሩር፣ “ደረት መሸፈኛ” ይባልም ነበር።