# ጥሩር ጥሩር የሚባለው በጦርነት ጊዜ ወታደሩን ለመከለል ደረትን የሚሸፍን መሥራሪያ ነው። እስራኤላዊው ሊቀ ካህን ይለብስ የነበረው ልዩ ዐይነት ልብስ ክፍል ጥሩር ይባል ነበር። * ወታደሮች የሚጠቀሙበት ጥሩር ከእንጨት፣ ከብረት ወይም ከቆዳ ነበር የሚሠራው። ዓላማው ቀስት፣ ጦር ወይም ሰይፍ የወታደሩን ደረት እንዳይወጋው መከላከል ነበር። * እስራኤላዊ ሊቀ ካህን የሚለብሰው ጥሩት ከጨርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የከበሩ ጌጣጌጦች ይያያዙበት ነበር። ቤተ መቅደሱ ውስጥ እግዚአብሔርን የማገልገል ሥራውን ሲያከናውን ካሁኑ ይህን ይለብስ ነበር። የሊቀ ካህኑ ጥሩር፣ “ደረት መሸፈኛ” ይባልም ነበር።