8 lines
1.1 KiB
Markdown
8 lines
1.1 KiB
Markdown
|
# ተሰሎንቄ፣ የተሰሎንቄ ሰዎች
|
||
|
|
||
|
አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ተሰሎንቄ በጥንቱ የሮም ግዛት ውስጥ የነበረችው የመቄዶንያ ዋና ከተማ ነበረች። በዚያ ከተማ የነበሩ፣ “የተሰሎንቄ ሰዎች” ይባላሉ።
|
||
|
|
||
|
* የተሰሎንቄ ከተማ በጣም ጠቃሚ ወደብ ነበረች፤ ሮምን ከተቀረው የሮም መንግሥት ጋር በሚያያዘው አውራ መንገድ ላይ ትገኝ ነበር።
|
||
|
* በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ጳውሎስ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ ጋር ወደ ተሰሎንቄ መጥተው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በዚያ በጣም እየሰፋች የነበረች ቤተ ክርስቲያን ተመሥርታ ነበር። በኋላም በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ጳውሎስ ይህችን ከተማ ጎብኝቷል።
|
||
|
* ጳውሎስ በተሰሎንቄ ለነበሩ ክርስቲያኖች መልእክቶች ጽፏል። የ1ኛና የ2ኛ ተሰሎንቄ መልእክቶች አዲስ ኪዳን ውስጥ ተካትተዋል።
|