am_tw/bible/names/stephen.md

11 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# እስጢፋኖስ
እስጢፋኖስ የመጀመሪያው ክርስቲያን ሰማዕት ማለትም በኢየሱስ በማመኑ የተገደለ የመጀመሪያ ሰው በመሆኑ ይበልጥ ይታወቃል። ሕይወቱንና አሟሟቱን የሚያመለክት ዝርዝር ሐዋርያት ሥራ የተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል
* እስጢፋኖስ ለመበለቶች ምግብና ለሌሎች ክርስቲያኖች የሚያስፈልገውን በማደል ክርስቲያኖችን እንዲያገለግል በጥንት ቤተ ክርስቲያን የተመረጠ ሰው ነበር
* እግዚአብሔርንና የሙሴን ሕጎች ተሳድበሃል በማለት አይሁድ እስጢፋኖስን በሐሰት ከሰሱት
* እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ከነበረው ግንኙነት ታሪክ በመጀመር እስጢፋኖስ በድፍረት ስለ ኢየሱስ እውነቱን ተናገረ
* የአይሁድ መሪዎች በጣም ታቆጡ፤ እስጢፋኖስን ከከተማ ውጪ በድንጋይ ቀጥቅጠው ገደሉት
* እርሱ ሲገደል በኋላ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የተባለው የጠርሴሱ ሳውል ይመለከት ነበር
* እስጢፋኖስ ከመሞቱ በፊት፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ኅጢአት አትቁጠርባቸው” በማለት በተነገረው የመጨረሻ ቃሉ በሚገባ ይታወቃል፤ ይህን ማለቱ ለሌሎች የነበረውን ፍቅር ያመለክታል