am_tw/bible/names/solomon.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ሰሎሞን
ሰሎሞን ከንጉሥ ዳዊት ልጆች አንዱ ነበር። የእናቱ ስም ቤርሳቤህ ይባል ነበር
* ሰሎሞን በነገሠ ጊዜ ከእርሱ ማንኛውንም ነገር እንዲለምን እግዚአብሔር ነግሮት ነበር። ስለዚህም ሰሎሞን ሕዝቡን በአግባቡና በፍትሕ ማስተዳደር የሚችልበት ጥበብ እንዲሰጠው ጠየቀ። ሰሎሞን በቀረበው ጥያቄ እግዚአብሔር ደስ ስለተሰኘ ጥበብንና ብዙ ሀብትን ሰጠው
* ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ለመሥራት ፈልጎ የነበረውን በኢየሩሳሌም የነበረውን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሠራ
* ምንም እንኳ ሰሎሞን በመጀመሪያው የአገዛዝ ዘመኑ በጥበብ ቢያስተዳድርም፣ በኋላ ግን በመታለል ባዕድ ሴቶች አገባ፤ አማልክቶቻቸውንም ማምለክ ጀመረ
* ሰሎሞን ታማኝነትን በማጉደሉ፣ ከእርሱ ሞት ብኋላ እስራኤላውያን ለሁለት መንግሥታት ተከፈሉ፤ እስራኤልና ይሁዳ። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ መንግሥታት እርስ በርስ ይዋጉ ነበር