am_tw/bible/names/rachel.md

8 lines
628 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ራሔል
ራሔል ከያዕቆብ ሚስቶች አንዷ ነበረች። እርሷና እኅቷ ልያ የያዕቆብ አጎት የላባን ልጆች ነበሩ።
* ራሔል ከእስራኤል ነገዶች ሁለቱ የሆኑት የዮሴፍና የብንያም እናት ነበረች።
* መጀመሪያ ላይ ራሔል ልጅ መውለድ አልቻለችም ነበር። ሆኖም፣ እግዚአብሔር ዮሴፍን መውለድ አስቻላት።
* ከዓመታት በኋላ ብንያምን በመውለድ ላይ እያለች ራሔል ሞተች፤ ያዕቆብም ቤተ ልሔም አጠገብ ቀበራት።