# ራሔል ራሔል ከያዕቆብ ሚስቶች አንዷ ነበረች። እርሷና እኅቷ ልያ የያዕቆብ አጎት የላባን ልጆች ነበሩ። * ራሔል ከእስራኤል ነገዶች ሁለቱ የሆኑት የዮሴፍና የብንያም እናት ነበረች። * መጀመሪያ ላይ ራሔል ልጅ መውለድ አልቻለችም ነበር። ሆኖም፣ እግዚአብሔር ዮሴፍን መውለድ አስቻላት። * ከዓመታት በኋላ ብንያምን በመውለድ ላይ እያለች ራሔል ሞተች፤ ያዕቆብም ቤተ ልሔም አጠገብ ቀበራት።