am_tw/bible/names/kingdomofisrael.md

7 lines
1.0 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# የእስራኤል መንግሥት
ንጉሥ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን በሁለት መንግሥታት ተከፈሉ። የእስራኤል መንግሥት አሥሩን ነገዶች የያዘው ሰሜናዊ መንግሥት ነበር።
* የእስራኤል መንግሥት ንጉሦች ሁሉ ክፉዎች ነበር። ሕዝቡ በኢየሩሳሌም ባለው ቤተ መቅደስ ማምለኩን እንዲተዉና ከዚያ ጣዖቶችንና ሐሰተኛ አማልክትን እንዲያመልኩ አሳምነውት ነበር። የኋላ ኋላ እንዲያጠቓችውና ብዙውን ሕዝብ እንዲማርኩ እግዚአብሔር እሦራውያንን ላከ።
* አሦራውያን በእስራኤል መንግሥት ከቀሩት ጥቂቶች ጋር አብረው እንዲኖሩ የሌላ አገር ሰዎችን ወደዚያ አመጡ። እነዚህ የሌላ አገር ሰዎች ከእስራኤላውያን ጋር ተጋብተው፣ ሳምራውያን የተባሉት ወገኖች ተገኙ።