10 lines
1.2 KiB
Markdown
10 lines
1.2 KiB
Markdown
|
# ኢዮኤል
|
||
|
|
||
|
ኢዮኤል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለውን ትንቢተ ኢዮኤል የጻፈ ነብይ ነበር፤ ትንቢተ ኢዮኤል የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ክፍል ከሆኑት አሥራ ሁለት አጫጭር ትንቢቶች አንዱ ነው።
|
||
|
|
||
|
* የነቢዩ ኢዮኤልን ግላዊ ታሪክ በተመለከተ ያለን መረጃ የአባቱ ስም ባቱኤል ይባል እንደነበረ ብቻ ነው።
|
||
|
* ከመጽሐፉ ይዘት መረዳት እንደሚቻለው ኢዮኤል የኖረውና ትንቢት የተናገረው የደቡባዊው የእስራኤል መንግሥት በነበረው በይሁዳ ነበር።
|
||
|
* ኢዮኤል የኖረውና ትንቢት የተናገረው መቼ እንደነበረ ግልጽ አይደለም፤ ሆኖም፣ የመጽሐፉን ይዘት መሠረት በማድረግ በንጉሥ ኢዮአስ ዘመን ሊሆን እንደሚችል አንዳንዶች ያስባሉ።
|
||
|
* በበዓለ ሃምሳ ቀን በሰበከው ስብከት ሐዋርያው ጴጥሮስ ከትንቢተ ኢዮኤል ጠቅሶ ነበር።
|
||
|
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢዮኤል የሚባሉ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ።
|