9 lines
1.2 KiB
Markdown
9 lines
1.2 KiB
Markdown
|
# ዕዝራ
|
||
|
|
||
|
ዕዝራ እስራኤላዊ ካህንና የአይሁድ ሕግ ሊቅ ነበር፤ ለ70 ዓመት በባቢሎን ምርኮ ከኖሩ በኋላ ወደኢየሩሳሌም የተመለሱ እስራኤላውያንን ታሪክ በጽሁፍ ያሰፈረ እርሱ ነበር።
|
||
|
|
||
|
* ዕዝራ ይህን የእስራኤል ታሪክ አንድ ክፍል በጽሁፍ ያሰፈረው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኘው መጽሐፈ ዕዝራ ነው። መጀመሪያ ላይ ሁለቱም እንደአንድ መጽሐፍ ይታወቁ ስለነበር መጽሐፈ ነህምያንም የጻፈው እርሱ ሊሆን ይችላል።
|
||
|
* ዕዝራ ወደኢየሩሳሌም ከተመለሰ በኋላ፣የሙሴን ህግ መጽሐፍ እንደገና ለሕዝቡ አስተዋወቀ፤ በዚያ ጊዜ እስራኤላውያን የሰንበትን ሕግ ማክበር ትተው ነበር፤ የአረማውያን ሃይማኖትን የሚከተሉ ባዕድ ሴቶች አግብተው ነበር።
|
||
|
* ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ሲቆጣጠሩ የደመሰሱትን ቤተመቅደስ እንደገና የሠራ ዕዝራ ነበር።
|
||
|
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዕዝራ በመባል የሚታወቁ ሰዎች ነበሩ።
|