am_tw/bible/names/cush.md

8 lines
800 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ኩሽ
ኩሽ የኖኅ ልጅ ካም ትልቁ ልጅ ነበር። የናምሩድ ጥንተ አባትም ነበር። ሁለቱ ወንድሞቹ ግብፅና ከነዓን ነበር።
* በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ “ኩሽ” ከእስራኤል በስተ ደቡብ የሚገኝ በጣም ሰፊ አካባቢ ነበር። ቦታው ስያሜውን ያገኘው ከካም ልጅ ከኩሽ እንደ ሆነ ይታሰባል።
* በጥንት ዘመን የኩሽ ምድር በተለያዩ ዘመን ውስጥ ሱዳንን፣ ግብፅን፣ ኢትዮጵያንና ምናልባትም ሳዑዲ አረቢያን ያጠቃልል ነበር።
* መዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ኩሽ የሚባል አንድ ሌላ ሰው ተጠቅሷል። ይህ ሰው ክብንያም ነገድ ነበር።