am_tw/bible/names/babylon.md

11 lines
1.8 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ባቢሎን፥ ባቢሎናዊ
የባቢሎን ከተማ የጥንት ባቢሎንያ አካባቢ ዋና ከተማ ሲሆን፥ የባቢሎን መንግሥት ግዛት አካልም ነበር
* ባቢሎን ትገኝ የነበረው ኤፍራጥስ ወንዝ አካባቢ ነበር፤ ከመቶ ዓመታት በፊት የባቢሎን ግንብ ተሠርቶ የነበረውም በዚሁ አካባቢ ነበር
* አንዳንዴ፥ “ባቢሎን” የተሰኘው ቃል የባብሎንን መንግሥት በሙሉ ያመለክታል። ለምሳሌ፥ “ የባቢሎን ንጉሥ” ያቺን ከተማ ብቻ ሳይሆን፥ በዚያ የነበረውን አካባቢ ሁሉ ይገዛ ነበር
* ባቢሎናውያን ኅያል ሕዝብ በመሆናቸው የይሁዳን መንግሥት አጥቅተው ነበር። ለ70 ዓመት ያህል ሕዝቡን በምርኮ ወደባቢሎን ወስደው ነበር
* የዚህ አካባቢ የተወሰነው ክፍል፥ “ከለድ” ሲባል፥ እዚያ የነበሩ ሕዝቦች “ከለዳውያን” ይባሉ ነበር። በዚህም ምክንያት፥ “ከለድ” የሚለው ቃል ባቢሎንን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል
* አዲስ ኪዳን ውስጥ፥ “ባቢሎን” የተሰኘው ቃል ከጣዖት አምልኮና ኃጢአተኛ ተግባሮች ጋር የሚያያዙ ቦታዎችን፥ ሕዝቦችንና የአስተሳሰብ ዘይቤዎችን ለማመልከት ተለዋጭ ዘይቤ በመሆን ጥቅም ላይ ውሏል
* “ታላቂቱ ባቢሎን” ወይም፥ “ታላቂቱ የባቢሎን ከተማ” የተሰኘው ሐረግ፥ ምሳሌያዊ ሲሆን መልኩ ልክ ጥንታዊቷ ባቢሎን እንደነበረችው በጣም ሰፊ ሀብታምና ኃጢአተኛ የሆን ከተማ ወይም ሕዝብን ያመለክታል።