# ባቢሎን፥ ባቢሎናዊ የባቢሎን ከተማ የጥንት ባቢሎንያ አካባቢ ዋና ከተማ ሲሆን፥ የባቢሎን መንግሥት ግዛት አካልም ነበር * ባቢሎን ትገኝ የነበረው ኤፍራጥስ ወንዝ አካባቢ ነበር፤ ከመቶ ዓመታት በፊት የባቢሎን ግንብ ተሠርቶ የነበረውም በዚሁ አካባቢ ነበር * አንዳንዴ፥ “ባቢሎን” የተሰኘው ቃል የባብሎንን መንግሥት በሙሉ ያመለክታል። ለምሳሌ፥ “ የባቢሎን ንጉሥ” ያቺን ከተማ ብቻ ሳይሆን፥ በዚያ የነበረውን አካባቢ ሁሉ ይገዛ ነበር * ባቢሎናውያን ኅያል ሕዝብ በመሆናቸው የይሁዳን መንግሥት አጥቅተው ነበር። ለ70 ዓመት ያህል ሕዝቡን በምርኮ ወደባቢሎን ወስደው ነበር * የዚህ አካባቢ የተወሰነው ክፍል፥ “ከለድ” ሲባል፥ እዚያ የነበሩ ሕዝቦች “ከለዳውያን” ይባሉ ነበር። በዚህም ምክንያት፥ “ከለድ” የሚለው ቃል ባቢሎንን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል * አዲስ ኪዳን ውስጥ፥ “ባቢሎን” የተሰኘው ቃል ከጣዖት አምልኮና ኃጢአተኛ ተግባሮች ጋር የሚያያዙ ቦታዎችን፥ ሕዝቦችንና የአስተሳሰብ ዘይቤዎችን ለማመልከት ተለዋጭ ዘይቤ በመሆን ጥቅም ላይ ውሏል * “ታላቂቱ ባቢሎን” ወይም፥ “ታላቂቱ የባቢሎን ከተማ” የተሰኘው ሐረግ፥ ምሳሌያዊ ሲሆን መልኩ ልክ ጥንታዊቷ ባቢሎን እንደነበረችው በጣም ሰፊ ሀብታምና ኃጢአተኛ የሆን ከተማ ወይም ሕዝብን ያመለክታል።