am_tw/bible/names/baasha.md

9 lines
815 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ባኦስ
ባኦስ እስራኤል ሐሰተኛ አማልክትን እንዲያመልኩ ካደረጉ የእስራኤል ነገሥታት አንዱ ነበር
* ባኦስ ሦስተኛው የእስራኤል ንጉሥ ሲሆን፥ አሳ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን ሃያ አራት ዓመት ገዝቷል
* ባኦስ ከእርሱ በፊት ንጉሥ የነበረውን ናዳብን በማግለል የነገሠ የጦር መሪ ነበር
* በባኦስ ንግሥና ዘመን በእስራኤልና በይሁዳ መንግሥት መካከል በተለይም ከይሁዳ ንጉሥ ከአሳ ጋር ብዙ ጦርነቶች ተደርገዋል
* ባኦስ ከፈጸማቸው ብዙ ኃጢአቶች የተነሣ የኋላ ኋላ እግዚአብሔር በሞት ከሥልጣኑ አስወገደው