am_tw/bible/kt/yahweh.md

12 lines
1.8 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ያህዌ
“ያህዌ” የእግዚአብሔር የተፀውዖ ስም ሲሆን፣ በሚቃጠለው ቁጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ የገለጠው በዚህ ስሙ ነበር።
* “ያህዌ” የሚለው ቃል የመጣው፣ “መሆን” ወይም፣ “መገኘት፣ ሐልዎት” ከተሰኙ ሁለት ቃሎች ነው።
* “ያህዌ” የሚለው ሌሎች አማራጭ ትርጕሞች፣ “እርሱ ነው” ወይም፣ “እኔ ነኝ” ወይም፣ “እንዲሆን የሚያደርግ” የተሰኙትንም ይጨምራል።
* ይህ ስም እግዚአብሔር ሁሌም የነበረ፣ አሁንም ያለና ለዘላለም የሚኖር መሆኑን ያመለክታል። እርሱ ሁሌም በቦታው ያለ መሆኑንም ያመለክታል።
* የአብዛኞቹ ዋና ዋና ቋንቋዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች፣ “ያህዌ” በሚለው ቃል ፈንታ፣ “ጌታ” በሚለው ቃል ተጠቅመዋል። ለምሳሌ፣ “እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ” የሚለው ቃል በቃል አገላለጽ፣ “እኔ አምላካችሁ ጌታ እግዚአብሔር ነኝ” ተብሏል።
* አንዳንድ ቤተ እምነቶች፣ “ያህዌ” ከማለት ይልቅ፣ “ጌታ” ማለትን አጥብቀው ይመርጣሉ።
* ይሁን እንጂ፣ ULB እና UDB የተሰኘው ትርጕም፣ ቃል በቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ባለው መሠረት የእግዚአብሔርን የተፀውዖ ስም ሁሌም ያህዌ በማለት ተርጉመዋል።
* “ያህዌ” የተባለው የተፀውዖ ስም አዲስ ኪዳን ውስጥ አይገኝም፤ ከዚያ ይልቅ ጥቅም ላይ የዋለው፣ “ጌታ” የተባለው ቃል ነው።