# ያህዌ “ያህዌ” የእግዚአብሔር የተፀውዖ ስም ሲሆን፣ በሚቃጠለው ቁጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ የገለጠው በዚህ ስሙ ነበር። * “ያህዌ” የሚለው ቃል የመጣው፣ “መሆን” ወይም፣ “መገኘት፣ ሐልዎት” ከተሰኙ ሁለት ቃሎች ነው። * “ያህዌ” የሚለው ሌሎች አማራጭ ትርጕሞች፣ “እርሱ ነው” ወይም፣ “እኔ ነኝ” ወይም፣ “እንዲሆን የሚያደርግ” የተሰኙትንም ይጨምራል። * ይህ ስም እግዚአብሔር ሁሌም የነበረ፣ አሁንም ያለና ለዘላለም የሚኖር መሆኑን ያመለክታል። እርሱ ሁሌም በቦታው ያለ መሆኑንም ያመለክታል። * የአብዛኞቹ ዋና ዋና ቋንቋዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች፣ “ያህዌ” በሚለው ቃል ፈንታ፣ “ጌታ” በሚለው ቃል ተጠቅመዋል። ለምሳሌ፣ “እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ” የሚለው ቃል በቃል አገላለጽ፣ “እኔ አምላካችሁ ጌታ እግዚአብሔር ነኝ” ተብሏል። * አንዳንድ ቤተ እምነቶች፣ “ያህዌ” ከማለት ይልቅ፣ “ጌታ” ማለትን አጥብቀው ይመርጣሉ። * ይሁን እንጂ፣ ULB እና UDB የተሰኘው ትርጕም፣ ቃል በቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ባለው መሠረት የእግዚአብሔርን የተፀውዖ ስም ሁሌም ያህዌ በማለት ተርጉመዋል። * “ያህዌ” የተባለው የተፀውዖ ስም አዲስ ኪዳን ውስጥ አይገኝም፤ ከዚያ ይልቅ ጥቅም ላይ የዋለው፣ “ጌታ” የተባለው ቃል ነው።