am_tw/bible/kt/ransom.md

7 lines
847 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ቤዛ
“ቤዛ” የሚለው ቃል በምርኮ የተያዘ ሰውን ለማስለቀቅ እንዲከፈል የተጠየቀ ገንዘብ ወይም ሌላ ነገር ያመለክታል።
* “ቤዛ መሆን” በባርነት ወይም በእስር ያለ ሰውን ነጻ ለማድረግ መክፈል ወይም ራስን መሥዋዕት ማድረግ ማለት ነው። ይህም፣ መልሶ መግዛት” ማለት ሲሆን፣ “መዋጀት” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጕም አለው።
* ኀጢአተኞችን ከኀጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት ቤዛ ለመሆን ኢየሱስ ራሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ። ለኀጢአታቸው ዋጋ በመክፈል እግዚአብሔር ሕዝቡን የመግዛቱ ተግባር በመጽሐፍ ቅዱስ “ቤዛነት” ይባላል።