am_tw/bible/kt/jealous.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ቀናተኛ፣ ቅናት
“ቀናተኛ” እና “ቅናት” የተሰኙት ቃሎች አንድ ሰው የግል የማድረግ ጽኑ ፍላጎት ያመለክታሉ። አንድን ነገር ወይም ንብረት አጥብቆ የመያዝ ፍላጎትንም ያመለክታል።
* ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሁለት አገላለጾች ጥቅም ላይ የሚውሉት ባል ሚስቱን ወይም ሚስት ባልዋን የግሏ ብቻ ለማድረግ የሚያሳዩት ጽኑ ፍላጎት ለማመልከት ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲሆን ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሁለት አገላለጾች ጥቅም ላይ የሚውሉት የእርሱ ሕዝብ ንጽሕና ማንኛውንም ኀጢአት እንዳያደርጉ እግዚአብሔር ያለውን ጽኑ ፍላጎት ለማመልከት ነው።
* እግዚአብሔርም ለስሙ፣ “ቀናተኛ” ነው፤ ስሙ እንዲከብርና እንዲፈራ ይፈልጋል።
* ሌላው ቅናት አሉታዊ ሲሆን ከራስ ይልቅ ሌላው ሲስካለትና ተወዳጅ ሆኖ ሲገኝ በቁጣ የሚገለጠው ነው። ይህ፣ “ምቀኝነት” ከሚለው ጋር በጣም የተያያዘ ነው።