# ቀናተኛ፣ ቅናት “ቀናተኛ” እና “ቅናት” የተሰኙት ቃሎች አንድ ሰው የግል የማድረግ ጽኑ ፍላጎት ያመለክታሉ። አንድን ነገር ወይም ንብረት አጥብቆ የመያዝ ፍላጎትንም ያመለክታል። * ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሁለት አገላለጾች ጥቅም ላይ የሚውሉት ባል ሚስቱን ወይም ሚስት ባልዋን የግሏ ብቻ ለማድረግ የሚያሳዩት ጽኑ ፍላጎት ለማመልከት ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲሆን ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሁለት አገላለጾች ጥቅም ላይ የሚውሉት የእርሱ ሕዝብ ንጽሕና ማንኛውንም ኀጢአት እንዳያደርጉ እግዚአብሔር ያለውን ጽኑ ፍላጎት ለማመልከት ነው። * እግዚአብሔርም ለስሙ፣ “ቀናተኛ” ነው፤ ስሙ እንዲከብርና እንዲፈራ ይፈልጋል። * ሌላው ቅናት አሉታዊ ሲሆን ከራስ ይልቅ ሌላው ሲስካለትና ተወዳጅ ሆኖ ሲገኝ በቁጣ የሚገለጠው ነው። ይህ፣ “ምቀኝነት” ከሚለው ጋር በጣም የተያያዘ ነው።