am_tw/bible/kt/foolish.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ሞኝ፣ ሞኝነት፣ ከንቱነት
“ሞኝ” የሚባለው ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ምርጫ የሚያደርግ በተለይም አለመታዘዝን የሚመርጥ ሰው ነው። “ሞኝነት” ማስተዋል የሌለው ሰው ወይም ፀባይ የሚገለጥበት መንገድ ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ፣ “ሞኝ” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር የማያምንና ለእርሱ የማይታዘዝ ሰውን ነው። ብዙውን ጊዜ ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውለው በእግዚአብሔር ከሚያምንናን ለእርሱ ከሚታዘዝ ሰው አንጻር ነው።
* መዝሙሮቹ ውስጥ ዳዊት በእግዚአብሔር የማያምንና በእግዚአብሔር ፍጥረቶች ውስጥ ያሉትን ማስረጃዎች ችላ የሚልን ሰው ሞኝ በማለት ይጠራዋል።
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፍ ምሳሌ ሞኝ ሰው ምን ማለት እንደ ሆነ ብዙ መገለጫዎች ያቀርባል።
* “ከንቱነት” ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ በመሆኑ ማስተዋል የሌለበት ድርጊት ያመለክታል።