# ሞኝ፣ ሞኝነት፣ ከንቱነት “ሞኝ” የሚባለው ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ምርጫ የሚያደርግ በተለይም አለመታዘዝን የሚመርጥ ሰው ነው። “ሞኝነት” ማስተዋል የሌለው ሰው ወይም ፀባይ የሚገለጥበት መንገድ ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ፣ “ሞኝ” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር የማያምንና ለእርሱ የማይታዘዝ ሰውን ነው። ብዙውን ጊዜ ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውለው በእግዚአብሔር ከሚያምንናን ለእርሱ ከሚታዘዝ ሰው አንጻር ነው። * መዝሙሮቹ ውስጥ ዳዊት በእግዚአብሔር የማያምንና በእግዚአብሔር ፍጥረቶች ውስጥ ያሉትን ማስረጃዎች ችላ የሚልን ሰው ሞኝ በማለት ይጠራዋል። * ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፍ ምሳሌ ሞኝ ሰው ምን ማለት እንደ ሆነ ብዙ መገለጫዎች ያቀርባል። * “ከንቱነት” ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ በመሆኑ ማስተዋል የሌለበት ድርጊት ያመለክታል።