am_tn/psa/089/049.md

3.1 KiB

ጌታ ሆይ፣ በእውነተኛነትህ ለዳዊት የማልክለት የቀድሞው የቃል ኪዳንህ ታማኝነት ወዴት አለ?

ጸሐፊው ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ጌታ ከዳዊት ጋር የገባውን ኪዳን እንዲጠብቅ ለመጠየቅ ነው፡፡"ጌታ ሆይ፣ በቀድሞው ጊዜ እንደ ነበርህ ከዳዊት ጋር የገባኸውን ኪዳን ጠብቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የቀደመው የቃል ኪዳን ታማኝነትህ ድርጊቶች

"ድርጊቶች" እና "ታማኝነት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች በግስ እና ተውሳከ ግስ መልካቸው ሊረተጎሙ ይችላሉ፡፡ "አስቀድሞ ያደረግሃቸው ነገሮች አንተ ለቃል ኪዳንህ ታማኝ መሆንህን ያሳያሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አስታውስ

ጸሐፊው ያህዌን ይህንን እንዲያስትውስ ይጠይቃል፡፡ "አስታውስ" ወይም "ስፍራ ስጠው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አገልጋችህ መቀለጃ ሆነናል

እዚህ ስፍራ "አገልጋዮችህ" የሚለው የሚያመለክተው የእስራኤልን ሰዎች ነው፡፡ "እንደምን በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ እንዳፌዙብን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እንደምን በልቤ ከአገራት ሁሉ እጅግ ብዙ ስድብን ተሸከምኩ

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚወክለው የሰውን ስሜቶች ነው፡፡ "ከአገራት ህዝቦች ብዙ ስድብን ተቋቋምኩ" ወይም "ከየአገራቱ ሰዎች በደረሰብኝ ስድብ ምክንያት ተሰቃየሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከየአገራቱ

እዚህ ስፍራ "አገራት" የሚለው የሚወክለው የተለያዩ አገራት ሰዎችን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ጠላቶች ስድብ አወረዱብኝ

ጠላቶች በንጉሱ ላይ በጩኸት መሳደባቸው የተገለጸው ስድብ ጠላቶች በንጉሡ ላይ በሀይል እንደሚወረውሩት ነገር/ቁስ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ በቀባኸው እርምጃዎች ላይ አፌዙ

እዚህ ስፍራ "እርምጃዎች" የሚለው የሚወክለው ንጉሡ የሄደበትን ነው፡፡ "የቀባኸውን በሄደበት እየተከተሉ አፌዙበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)